Announcements

EMPOWERING EDUCATORS ፡Generative AI and cloud computing technology transfer ስልጠና በመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ
ግንቦት 08/2017
…………………………
በመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ EMPOWERING EDUCATORS: Generative AI and cloud computing technology transfer training for Academicians ’በሚል ርእስ ለመምህራንና እና ለአስተዳደር ሰራተኞች ስልጠኛ ተሰጠ፡፡
ለአምስት ተከታታየ ቀናት በተሰጠው በዚህ ስልጠና ላይ ከሮቤ እና ጎባ ካምፓሶች ከተለያዩ ኮሌጆች ለተውጣጡ ሀምሳ መምህራንና አስር የአስተዳደር ሰራተኞች ናቸው ስልጠናውን የወሰዱት፡፡
የስልጠው ዋና ዋና አላማዎች ውስጥ/ Arteficial intelligence /ሰው ሰራሽ አስተውሎትን ከመማር ማስተማር ስራው ጋር ማቀናጀት አብሮ ማስኬድ እና መጠቀም የሚቻልበትን ሁኔታ አስቻይ አቅም መፍጠር የሚቻልበትን ግንዛቤ ማስጨበጥ ብሎም ለጥናትና ምርምር ስራዎች አጋዥ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ እና ሌሎች የኮምፒውተር ሶፍተዌሮችን መምህራን መጠቀም እንዲችሉ የሚያስችል እና ስራዎችን ለማቀላጠፍ እንዲያግዝ የማድረግ ኣላማ ያለው ስልጠና እንደሆነ ተገልፅዋል፡፡
የቴክኖሎጂ ሽግግር እና ማህበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ከኮምፒቲንግ ኮሌጅ ጋር በቅንጅት የተሰጠ ስልጠና ሲሆን በቀጣይ ለአራት መቶ /400/ ለሚሆኑ መምህራን ይህንን ‘’Generative AI and cloud computing technology transfer’’ ስልጠና ለመስጠት መታቀዱም ተገልፅዋል፡፡
በስልጠናው ማጠናቀቂያ ላይ ንግግር ያደረጉት የመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ቴክ/ሽግግር እና ማህበረሰብ አገልግሎት
ዳይሬኮቶሬት ዳይሬክተር ዶ/ር ሙሃመድ ጀማል በሰልጠናው ያገኛችሁትን እውቀት እንዴት ወደ ራሳችሁ መስክ በመውሰድ
ትጠቀሙበት እና ልታጎለብቱት ይገባል፡፡ሰው ሰራሽ አስተውሎት በያንዳንዱ የህይወታችን መስመሮቻችን ልናውቀው እና
ልንጠቀምበት በማንኛውም ሁኔታ ከጌዜው ጋር አብሮ ለመራመድ ሊኖረን የሚገባ ከዘመኑ ቴክኖሎጂዎች ውስጥ
የሚመደብ ህይወታችንን ሊለውጥ ሊያዘምን የሚችል በመሆኑ ልትጠቀሙበት ብሎም ልታጎለብቱት ይገባል በማለት
መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
በስልጠናው ማጠቃለያ ላይ ለሰልጣኖች እንዲሁም የምስክር ወረቀት ተሰትዋቸዋል፡፡
ልህቀት በብዝሃነት !
መደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ
ህዝብ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት
ባሌ ሮቤ
ለተጨማሪ መረጃ
ስልክ 0222441361/228902110